የታካሚ የፋይናንስ አገልግሎቶች ጽ/ቤት

ይህንን ገፅ በአማርኛ አውርድልኝ

ጽሕፈት ቤት፥

የታካሚ ሒሳብ ባለጉዳይ አገልግሎት

ፖሊሲ አርእስት፥

የፋይናንስ እርዳታ

የፖሊሲ ቁጥር፥

PFS.5000.1

ዓላማ፥

የአሰራር ደንቡ፣ በትክክል-የተገለጸ፣ ታካሚ ያለበትን ቀሪ ዕዳ እንዲከፈል የማያደረግ ኢንዱስትሪው የሚከተለው መደበኛ ፕሮቶኮልን በዝርዝር ያስቀምጣል። የአሰራር ደምቡ፣ ከታካሚው ሒሳቦች ዕዳ ስብሰባና ወደ ውጭ ሰብሳቢ ኤጀንሲ ሒሳቦቹን ከመምራት ጋራ የሚዛመድ ያልተዛባ ሂደትንና የኦዲት ተግባሮችን በዝርዝር ይገልጻል።

የታካሚው (ወይም በኃላፊነት ተጠያቂው ወገን) የግል የፋይናንስ ኃላፊነት የሆኑትን ቀሪ ዕዳዎች ለመሰብሰብ Valley Medical Center ተገቢውን ጥረት ያደርጋል።  ሐኪም ቤቱ ማድረግ በሚችለው መንገድ ሁሉ ያልተከፈሉ ዕዳዎችን ለመሰብሰብ ጥረት ካደረገ በኋላ ሳይከፈሉ የሚቀሩ ዕዳዎች፣ ለተሰጠው እንክብካቤ ክፍያውን ለማስከፈል ተጨማሪ እርምጃ ወደሚያደርጉ የውጭ ፕሮፌሽናል ሰብሳቢ ኤጀንሲዎች ይተላለፋል።

 

የአሰራር ደንብ፥

አጠቃላይ በገዛ-ራስ ክፍያ ስቴትመንት የግዜ ሰንጠረዥ

የመጀመሪያ ስቴትመንት

ቀን 1

ሁለተኛ ስቴትመንት

ቀን 31

ሁለተኛ ስቴትመንት

ቀን 61

የመጨረሻ ማስታወቅያ

ቀን 91

የመጥፎ ዕዳ ቅድመ-ዝርዝር ግምገማ

ቀን 115

መጥፎ ዕዳ ማራገፍ

ቀን 120

 

አጠቃላይ የስራ መርሆች፥

  1. የሕክምና ወጪዎች፣ የተወሰነ ወይም ምንም የጤና እንክብካቤ ከፋይ ለሌላቸው ታካሚዎች ምንኛ ሸክም ሊሆን እንደሚችል እንገነዘባለን። የመድን ዋስትና ለሌላቸው ታካሚዎች፣ ልክ ለተኮናተርናቸው የመድን ዋስትና አቅራቢዎች የምንሰጠውን ቅናሽ ያህል እንሰጣቸዋለን።
     
  2. የመድን ዋስትና ለሌላቸው ታካሚዎች፣ ለቀሪ ዕዳቸው ወዲያዉኑ የሚከፍሉበት የቅናሽ ክፍያ አማራጭ ይሰጣቸዋል።  (እባክዎ ኢንሹራንስ የሌላቸው እና የወዲያው ክፍያ ቅናሽ ፖሊሲን (Uninsured & Prompt Pay Discount) ይመልከቱ።)
     
  3. ጠቅላላውን ዕዳ በአንድ ላይ መክፈሉ በጣም እንደሚያስቸግራቸው ለሚያሳወቁ ታካሚዎች ወይም በኃላፊነት ተጠያቂ ወገኖች፣ እስከ 12 ወራት ድረስ የሚደርስ ከወለድ ነጻ ክፍያ የሚከፍሉበት የክፍያ መንገድ ይቀርብላቸዋል። አነስተኛው የክፍያ መጠን የሚሆነው $50 ለሁሉም የሐኪም ቤት ሒሳቦች እንዲሁም $25 ለሁሉም የሐኪም ሒሳቦች፣ የጊዜው ርዝመት ከ 12 ወራት መብለጥ የለበትም። ታካሚ ወይም በኃላፊነት የሚጠየቀው ወገን፣ ሙሉን ክፍያ ለመክፈል ይህን የ 12 ወራት ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ካልቻለ፣ የባንክ ፋይናንስ ይቀርብላቸዋል።
     
  4. Valley Medical Center፣ በባንክ ባልደረባ በኩል የረጅም ግዜ የክፍያ ዕቅድ አማራጮችን ያቀርባል። (ልክ እንደ ማንኛውም የባንክ ዕዳ ወይም ክረዲት ካርድ፣ ብድሩ ወለድ የሚያከማችና ክፍያዎች በግዜያቸው ካልተከፈሉ፣ ዘግይቶ ከፋይን መቀጮ የሚያስከፍሉ ይሆናሉ)።
     
  5. ታካሚው በገቢ እጥረት ምክንያት ቢሉን በጭራሽ መክፈል እንደማይችል ካሳወቀ፣ ለታካሚው ወይም በኃላፊነት የሚጠየቀው ወገን የፋይናንስ እርዳታ ማመልከቻ ይሰጠዋል፣ ይህም ማመልከቻ ተሞልቶ ከተገቢዎቹ ደጋፊ ሰነዶች ጋራ ለሒሳቡ ቀሪ ዕዳ ማስተካከያ የፋይናንስ እርዳታ ጉዳዩ እንዲጠና መመለስ ይኖርበታል። (እባክዎ የፋይናንስ እርዳታ ፖሊሲን ይመልከቱ)
     
  6. Valley Medical Center መመዘኛዎችን ለሚያሟሉ የኪንግ ካውንቲ የመንግስት ሐኪም ቤት ዲስትሪክት .1 (King County Public Hospital District #1) የቤት ባለንብረቶች ለሚከፈሉት የንብረት ታክስ፣ የቫሌ የታክስ ክፍያ ድርሻ (Valley Tax Dividend) ማስተካከያ ያቀርብላቸዋል። Valley የክፍያ ድርሻ (Dividend) ክሬዲት፣ ሁሉም የሶስተኛ ወገንና የመድን ዋስትና ክፍያዎች ተደርገው ካበቁ በኋላ ለሚቀረው ዕዳ ከኪስ-ለሚከፈሉ ወጪዎች ሊውል ይችላል።

    የማስተካከያው መጠን የሚወሰነው፣ በኪንግ ካውንቲ ታክስ (King County Tax) የይፋ መዝገብ መሰረት ለሐኪም ቤት ዲስትሪክት ቁጥር 1 (Hospital District Number) በተመደበው የታክስ ክፍያ መጠን ነው። ማንኛውም የሐኪም ቤት ዲስትሪክት .1 (Hospital District #1) ነዋሪ በህይወት ዘመኑ የሚያገኘው Valley ታክስ ክፍያ ድርሻ ማስተካከያ (Tax Dividend Adjustment) ከፍተኛው መጠን $3,000 ነው።

     
  7. ክፍያቸውን በቼክ/ ክሬዲት/ ደቢት ካርድ የሚከፍሉ ታካሚዎች ወይም በኃላፊነት የሚጠየቁ ወገኖች፣ በቂ ገንዘብ ባለ መኖሩ ምክንያት ክፍያው ተመላሽ ከሆነ፣ በሒሳባቸው ላይ ተጨማሪ NSF ክፍያ ይደመርባቸዋል። በአሁኑ ወቅት Valley Medical Center በቂ ገንዘብ ባለመኖሩ ምክንያት ለሚመለስ ማንኛውም የቼክ ወይም ክሬዲት/ደቢት ካርድ ክፍያ፣ $ 35.00 ያስከፍላል።
     
  8. ቫሊይ የህክምና ማዕከል (Valley Medical Center) ከመጀመሪያ መግለጫው በኋላ ባሉ 30 ቀናት እና ከዚያ በኋላ በየወሩ የግል-ከፋይ መግለጫ ባላቸው የሂሳብ ቁጥሮች ላይ 1% የወለድ ተመን ያስከፍላል። በክፍያ ዕቅዶች ላይ ያሉ፣ ወይም ግምገማ ላይ ያሉ ወይም እየተጠባበቁ ያሉ መለያዎች ወደ የግል-ከፋይ ኡደት እስከሚመለሱ ድረስ ወለድ አይከፍሉም።
     
  9. Valley Medical Center የግል ከፍይ ዕዳ ስብሰባ ጥረቶች የሚካሄዱት በዋሽንግተን ስቴት የስራ አፈጻጸምና Medicare / Medicaid መመሪያዎች መሰረት ነው።
     
  10. የሕክምና ዕዳ መያዣዎች፥

    አንድ ታካሚ የአደጋ ወይም  የመጥፎ ተግባር ሰለባ ከሆነ፣ የመድን ዋስትናው ሌላ ወገን ለጉዳዩ ተጠያቂ እንደሚሆን ከተወሰነ በኋላ አብዛኛውን ግዜ ለሕክምና አገልግሎቶች ክፍያ አያደርግም። በተጨማሪም፣ አንድ ታካሚ የመድን ዋስትና ላይኖረው ይችል ይሆናል፣ ቢሆንም በኃላፊነት ከሚጠየቀው ወገን ካሳ እንዲከፈለው በመጠየቅ ላይ ሊሆን ይችላል። በእነዚህ ሁኔታዎች ላይ፣ ወደፊት ለአካል ጉዳት ካሳ በሚከፈለው ክፍያ ስምምነት ላይ UW/Valley Medical Center የዕዳ መያዣ እንዲደረግ ጥያቄ ሊያቀርብ ይችላል። የዕዳ መያዣ ሲባል፣ ዕዳ መከፈሉን ለማረጋገጥ፣ በአንድ ሰው ቤት-ንብረት ወይም የግል ንብረት ላይ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረቢያ መንገድ ነው።

     
  11. ወደ ሰብሳቢ የተዛወረ ሒሳብ ሊያጠቃልል የሚችለው፥
  • ከሐኪም ቤት ወጥተው የመጀመሪያው ቢል ከተላከበት 300 ቀኖች በኋላ ስለ ክሬዲት ሪፖርት ይደረጋል።
  • ሳይከፈል ግዜ ላለፈበት ቢል፣ ከሐኪም ቤት ከወጣ የመጀመሪያው ቢል መግለጫ ከተላከበት 240 ቀኖች በፊት ክስ ላይመሰረት ይችላል።
  • የስልክ ጥሪዎች።
  • ሕጋዊ ውሳኔን ተከትሎ የደሞዝ ተቆራጭ ማድረግ።
  • የሕክምና ዕዳ መያዣዎች።
  • Valley Medical Center በማንኛውም ሒሳብ ላይ ለሚወሰዱ ማናቸውም ሕጋዊ እርምጃዎች ፈቃድ መስጠት አለበት።
  • Valley Medical Center ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው ሁነኛ ሥራ ከሌለው ክስ እንዲመሰረት ፈቃድ አይሰጥም።
  • ሒሳቦች በአንድ ኤጀንሲ ለአንድ ዓመት ለምደባ ይተላለፉና፣ ከዚያ በኋላ የክፍያ መንገድ ስምመነት ላይ ካልተደረሰ ወይም ሕጋዊ ፍርድ ካልተሰጠ፣ በሌላ ኤጀንሲ ለሁለተኛ ምደባ ይተላለፋሉ።
  • በቀድሞዎቹ 90 ቀኖች ውስጥ ምንም ድርጊት ካልነበራቸው የሁለተኛ ምድብ ሒሳቦች ከአንድ ተጨማሪ ዓመት በኋላ እንዲመለሱ ይደረጋሉ።
  • ለሁለተኛ ምድብ ተላልፈው የነበሩ ሒሳቦች ሊሰበሰቡ እንደማይቻሉ ተቆጥረው ኤጀንሲው ሊሰበስባቸው የማይችላቸው ሆነው ማስተካከያ ይደረግባቸዋል።
  • ያልተከፈሉ ቀሪ ዕዳዎች በዋሱ የክሬዲት ታሪክ ላይ ለሰባት ዓመት ወይም ደግሞ ሕጋዊ ማስተካከያ ከነበረ ለአስር ዓመት ይቆያሉ።
     

የጤና እንክብካቤ መድን ዋስትና ሽፋን የሌላቸው ታካሚዎች

  1. የጤና እንክብካቤ መድን ዋስትና ሽፋን የሌላቸው Valley Medical Center ታካሚዎች፣ ላገኙት እንክብካቤ ምን ያህል ዕዳ እንዳለባቸው የሚያሳይ የስቴትመንት አጭር ዝርዝር፣ ከሐኪም ቤት ከወጡ በኋላ በግምት 5 ቀን ውስጥ ይላክላቸዋል። ስለ ፋይናንስ አማራጮች ለመወያየት የሚያስፈልግ መረጃ፣ ከባለ ጉዳይ የአገልግሎት /ቤት ጋራ ከመገናኛ መረጃ ጋራ አብሮ ቀርቧል።

    ማሳሰቢያ Valley Medical Center የጤና እንክብካቤ ሽፋን ለሌላቸውና ሐኪም ቤት እንዲገቡ ለተደረጉ ታካሚዎች Medicaid ማመልከቻን ለመሞላት እርዳታ ያደርጋል።  ታካሚዎች Medicaid ብቁ መሆናችውን ለማወቅ ማጣሪያ ይደረግላቸውና፣ እንደተገቢነቱ ለማመልከቻው ሂደት እርዳታ ይደረግላቸዋል።

     
  2. ታካሚዎች ካላቸው ዕዳ ላይ 30 በመቶ ወዲያዉኑ ለተከፈለው ቅናሽ  ለማግኘት ብቁ ናቸው።
     
  3. ቫሊ ለታካሚው ወይም ክፍያውን የመክፈል ኃላፊነት ላለበት ወገን 4 የሒሳብ መግለጫ ማስታወቂያዎችን በመላክ ስለ ቀሪው ያልተከፈለ ሒሳብ ያሳውቃቸዋል። የክፍያ አማራጮችን መሰረት በማድረግ፣ ከመጀመሪያው የመግለጫ ቀን በኋላ ካሉት 14 ቀናት ጀምሮ ታካሚዎች የስልክ ጥሪዎች፣ የጽሁፍ መልዕክቶች፣ ወይም የ MyChart ማሳወቂያዎች ሊደርሷቸው ይችላሉ። 
     
  4. ክፍያው ሙሉ በሙሉ ካልተከፈለ፣ ወይም የክፍያው  አከፋፈል  ስምምነት ላይ ካልተደረሰ፣ ከስቴትመንቱ ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ቀሪው ዕዳ ሙሉ በሙሉ ካልተከፈለ ወይም የክፍያው አከፋፈል ስምምነት ላይ ካልተደረሰ፣ ዕዳውን ለመሰብሰብ ተጨማሪ ጥረት ይደረግ ዘንድ ሒሳቡን ከመምራት በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌለ የሚ ገልጽ የመጨረሻ የቅድመ-ዕዳ ስብሰባ ማስታወቅያ በኃላፊነት ለሚጠየቀው ወገን ይላካል።
     
  5. ክፍያው ሙሉ በሙሉ ካልተከፈለ፣ ሌሎች የክፍያው አከፋፈል ስምምነቶች ከተዘጋጁ፣ ሒሳቡ 120 ቀን የሒሳብ ዙርን ካሟላ፣ እና ሁሉም መስፈርቶች ከተሟሉ፣ ሒሳቡ ወደ ፕሮፌሽናል ሰብሳቢ ኤጀንሲ ይተላለፋል።
     

የጤና እንክብካቤ የመድን ዋስትና ሽፋን ያላቸው ታካሚዎች

  1. Valley Medical Center መኖራቸው  የታወቁትን የመድን ዋስትና ሰጪዎችን ሁሉ ቢል ያደርጋል። Valley Medical Center እና በከፋዩ መካከል ኮንትራት በሚኖር ግዜ፣ ታካሚውን በሒሳቡ ውስጥ ያለውን ቀሪ ዕዳ እንዲከፍል ከመጠየቁ በፊት Valley Medical Center ከተቀዳማ ከፋዩና ከሁለተኛው ከፋይ ክፍያው እስከሚከፈለው ድረስ ይጠብቃል።  
     
  2. ቫሊ የሕክምና ማዕከል (Valley Medical Center) ከኢንሹራንስ ኩባንያ(ዎች) ምላሽ ካገኘ በኋላ ለታካሚው ቀሪ ሒሳቦች መግለጫ የሒሳብ ሰነድን ያዘጋጃል። ሁሉም እንዲከፈሉ የሚጠበቁ ክፍያ (ክፍያዎች) ከተከፈሉ በኋላ፣ ቫሊ ለታካሚው ወይም ክፍያውን የመክፈል ኃላፊነት ላለበት ወገን 4 የሒሳብ መግለጫ ማስታወቂያዎችን በመላክ ስለ ቀሪው ያልተከፈለ ሒሳብ ያሳውቃቸዋል። የክፍያ አማራጮችን መሰረት በማድረግ፣ ከመጀመሪያው የመግለጫ ቀን በኋላ ካሉት 14 ቀናት ጀምሮ ታካሚዎች የስልክ ጥሪዎች፣ የጽሁፍ መልዕክቶች፣ ወይም የ MyChart ማሳወቂያዎች ሊደርሷቸው ይችላሉ። 
     
  3. ክፍያ ሙሉ በሙሉ ካልተከፈለ፣ ወይም የክፍያው አከፋፈል ስምምነት ላይ ካልተደረሰ፣ ከስቴትመንቱ ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ቀሪው ዕዳ ሙሉ በሙሉ ካልተከፈለ ወይም የክፍያው አከፋፈል  ስምምነት ላይ ካልተደረሰ፣ ዕዳውን ለመሰብሰብ ተጨማሪ ጥረት ይደረግ ዘንድ ሒሳቡን ለሰብሳቢ ከመምራት በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌለ የሚገልጽ የመጨረሻ የቅድመ-ዕዳ ስብሰባ ማስታወቅያ ለታካሚው ወይም በኃላፊነት ለሚጠየቀው ወገን ይላካል።
     
  4. ክፍያው ሙሉ በሙሉ ካልተከፈለ ወይም ሌሎች የክፍያው አከፋፈል ስምምነቶች ከተዘጋጁ፣ ሒሳቡ 120 ቀን የሒሳብ ዙርን ካሟላ፣ እና ሌሎች ሁሉም መስፈርቶች ከተሟሉ፣ ሒሳቡ ሐኪም ቤቱ ወደ ተኮናተረው ፕሮፌሽናል ሰብሳቢ ኤጀንሲ ይተላለፋል።